ወልዋሎዎች ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ተስማሙ

ሁለት ተጫዋቾች ቢጫዎቹን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሰዋል።

ቀደም ብለው በረከት አማረ፣ ሰለሞን ጌታቸው እና ጋናዊው ቃሲም ራዛቅን ለማስፈረም የተስማሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት በሸገር ሲቲ ያሳለፉት ሁለት ተጫዋቾች የግላቸው ለማድረግ ተስማምቷል።

ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው የመጀመርያው ተጫዋች አላዛር ሽመልስ ነው። የእግር ኳስ ህይወቱን ከአዲስ አበባ ከተማ የጀመረው ይህ የመስመር አጥቂ በዋናው ቡድን ደረጃ ለአሳዳጊ ክለቡ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ መጫወት የቻለ ሲሆን ስምንት ግቦች ባስቆጠረበት የባለፈው የውድድር ዓመት ደግሞ ከከፍተኛ ሊጉ ሸገር ከተማ ጋር አሳልፏል። ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአስራ ሰባት ዓመት በታች እና ሀያ አንድ ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ማገልገል የቻለው ተጫዋቹ ቢጫዎቹን ለመቀላቀል መስማማቱን ተከትሎ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚመለስ ይሆናል።

ሁለተኛው ቢጫዎቹን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ደግሞ ሚራጅ ሰፋ ነው። የቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ውጤት የሆነው ይህ አማካይ ለፈረሰኞቹ ታዳጊና ዋና ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ ወልዋሎ ለመቀላቀል ተስማምቶ ዳግም በፕሪምየር ሊጉ የምናየው ይሆናል።