ኢትዮ ኤሌክትሪክ አጥቂ ለማስፈረም ተስማማ

ዳግም ወደ ሊጉ የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የፊት አጥቂ ለማስፈረም ተስማምቷል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን በትናትናው ዕለት በይፋ አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ዝውውሩ በመግባት የነባር ተጫዋቾቹን ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እየቀላቀለ ይገኛል።

ለቡድኑ ለመጫወት የተስማማው የፊት መስመር አጥቂው ፍቃዱ አለሙ መሆኑ ታውቋል። በአዲስ አበባ ከተማ ፣ መቻል እና ያለፉትን አራት ዓመታት በዐፄዎቹ ቤት ቆይታ ካደረገ በኋላ አሁን መዳረሻው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሆኖ ለሁለት አመት ለመጫወት ተስማምቷል።

ከፊት ባሉት ቀናቶች አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታው የሌሎች ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው እንደሚቀላቀሉ ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።