ኢትዮ ኤሌክትሪክ የመስመር ተጫዋቹን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

ሽመክት ጉግሳ ከስድስት ዓመታት የፋሲል ከነማ ቆይታ በኋላ አዲስ አዳጊውን ክለብ ተቀላቀሏል።

ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ወደ ፕሪምየር ሊጉ መመለሳቸውን ተከትሎ በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በርከት ያሉ ተጫዋቾች በማስፈረም የሚገኙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አሁን ደግሞ የመስመር ተጫዋቹ ሽመክት ጉግሳ አስፈርመዋል። በ2011 ደደቢት ለቆ ወደ ዐፄዎቹ ቤት በማምራት ላለፉት ስድስት ዓመታት በወጥነት ያገለገለው ይህ ተጫዋች ፋሲል ከነማ የፕሪምየር ሊግና የኢትዮጵያ ዋንጫን ስያነሳ ጉልህ አስተዋጾ አበርክቷል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ ወላይታ ድቻ፣ አየር ኃይል፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት፣ ከ2011 ጀምሮ ደግሞ በፋሲል ከነማ መለያ ያሳለፈው ሽመክት በዚህ ዝውውር መስኮት ኤሌክትሪክ የተቀላቀለ ሦስተኛ የፋሲል ከነማ ተጫዋች ሆኗል።