ምዓም አናብስት ስብስባቸውን ማጠናከር ተያይዘውታል

መቐለ 70 እንደርታ አማካዩን ለማስፈረም ተስማማ።

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ከሚገኙ ክለቦች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው መቐለ 70 እንደርታ በዝውውር መስኮቱ አስረኛ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል። ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው ደግሞ ባለፈው የውድድር ዓመት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያሳለፈው የተከላካይ አማካዩ ሄኖክ አንጃው ነው። በብርቱካናማዎቹ ቤት የውድድር ዓመት ቆይታው በአስራ ስምንት ጨዋታዎች ተሳትፎ 1311 ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው አማካዩ ከዚህ ቀደም በቡታጅራ ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ መድን ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ ፣ ገላን ከተማ እና በኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ መጫወቱ ይታወሳል ፤ ቀሪ የወረቀት ስራዎች ሲያልቁም በይፋ የመቐለ 70 እንደርታ ተጫዋች ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ተጫዋቹ መቐለን ለመቀላቀል መስማማቱን ተከትሎ ከሸሪፍ መሐመድ፣ ያሬድ ከበደ ፣ ሶፎኒያስ ሰይፈ፣ ያሬድ ብርሀኑ፣ ሠለሞን ሀብቴ፣ ቦና ዓሊ ፣  መናፍ ዐወል፣ ተመስገን በጅሮንድ እና አልፋ ሴሳይ ቀጥሎ ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማ አስረኛ ተጫዋች ሆኗል።