ፈረሰኞቹ የቀድሞ አሰልጣኛቸውን ዳግም አግኝተዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በይፋ ሾሟል።

ለ2017 የውድድር ዘመን አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት ፈረሰኞቹ የቀድሞ አሰልጣኛቸውን ፋሲል ተካልኝን ዳግም ከዓመታት በኋላ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ከተጫዋችነት እስከ አሰልጣኝነት ብዙ ስኬቶችን አብሮ ማሳለፍ የቻለው አሰልጣኝ ፈሲል ተካልኝ በስልጠና ህይወቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በመቀጠል በባህር ዳር ከተማ ፣ በአዳማ ከተማ እና በመቻል ቆይታ ካደረገ በኋላ ዳግም ወደ ቤቱ መመለሱን ክለቡ ይፋ አድርጓል።