መቻሎች ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማሙ

በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚመሩት መቻሎች የግብ ዘቡን የክረምቱ ስድስተኛ ፈራሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በክረምቱ የዝውውር ገበያ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት አማኑኤል ዮሐንስ ፣ አብዱልከሪም ወርቁ እና ዓለምብርሀን ይግዛውን ከፕሪምየር ሊግ ክለቦች ዳንኤል ዳርጌ እና ፊልሞን ገብረፃዲቅን ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ቡድናቸው ያመጡት እና የከነዓን ማርክነህ ፣ በረከት ደስታ ፣ ደሳለኝ ከተማ ፣ ምንይሉ ወንድሙ ፣ ዳዊት ማሞ እና ነስረዲን ኃይሉን ውል ያራዘሙት መቻሎች በዛሬው ዕለት ደግሞ ስድተስኛ ፈራሚ ተጫዋቻቸው የግብ ዘቡ ምንታምር መለሠ ሆኗል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በ11 የሊጉ ጨዋታዎች ለሀምበሪቾ 990 ደቂቃን ተሰልፎ የተጫወተው ግብ ጠባቂው የመጀመሪያ ክለቡ ከሆነው ሺንሺቾ ከተማ ጋር ከተለያየ በኋላ ላለፉት ሦስት ተከታታይ የውድድር ዓመታት ከሀምበሪቾ ጋር ከከፍተኛ ሊጉ እስከ ፕሪምየር ሊጉ ካገለገለ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው መቻል ሆኗል።