ቡርትካናማዎቹ ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የግብጠባቂውን ውል አራዝመዋል

ወደ ዝውውሩ የገቡት ድሬደዋ ከተማዎች ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የግብጠባቂያቸውን ውል አራዝመዋል።

አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን በይፋ ከሾሙ በኋላ ወደ ዝውውሩ የገቡት ድሬደዋ ከተማዎች አስቀድመን ባጋራናቹሁ መረጃ መሰረት የአህመድ ረሺድን ዝወረውር ይፋ ያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው በመቀላቀል የግብጠባቂያቸውን ውል ማራዘማቸውን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

አጥቂው መሐመድ ኑር ናስር ቡድኑን የተቀላቀለ ተጫዋች ሲሆን በኢትዮጵያ መድን የእግርኳስ ህይወቱን መነሻ በማድረግ እስከ ዋናው ቡድን ከተጫወተ በኋላ በጅማ አባ ጅፋር እና የለፉትን ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል።

የረመዳን የሱፍ ታናሽ ወንድም የሆነው እና በክልል ክለቦች ሻምፒዮን አሶሳ ከተማን በመወከል ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በሀምበሪቾ ከተማ ቆይታ የነበረው የግራ መስመር ተከላካይ አብዱልሰላም የሱፍ ማረፊያው የምስራቁ ክለብ ድሬደዋ ከተማ ሆኗል።

በቡድኑ ውሉን ያራዘመው ወጣቱ ግብጠባቂ አብዩ ካሳዬ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጫወት ዕድል ካከገኘ በኋላ በአግባቡ እድሉን የተጠቀመ ሲሆን ከአሳዳጊ ክለቡ ጋር ለተጨማሪ ዓመታት ለመቆየት ፊርማውን አኗሯል።

ሦስቱምት ተጫዋቾች ለሁለት አመት ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን በቀጣይ ቀናቶች ቡርትካናማዎቹ ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው እንደሚቀላቅሉ ይጠበቃል።