የ2017 የውድድር ዘመን የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳል

በአስራ ዘጠኝ ቡድኖች የሚሳተፉበት የቀጣይ ዓመት የውድድር ዘመን የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብረ በቀጣይ ሳምንት ይከናወናል።


አክስዮን ማህበር ከተቋቋመ ጊዚ ጀምሮ በርከት ያሉ ጨዋታዎችን እንደሚስተናገድበት የሚጠበቀው የ2017 የውድድር ዘመን በአስራ ዘጠኝ ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ ይታወቃል። የቀጣይ ዓመት ውድድርን በተሻለ ሁኔታ ለማስኬድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው አክስዮን ማህበሩ በቀጣይ ሳምንት ባሉት ቀናት ውስጥ የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብሩ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ይሆናል።

በሳምንት ዘጠኝ ጨዋታዎች አንድ ቡድን አራፊ እያደረገ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው የቀጣይ ዓመት የሊጉ ውድድር አንድ ቡድን በዓመት ውስጥ በሁለት ዙር የተከፈለ 36 ጨዋታዎች የሚያደርግ ሲሆን በአጠቃላይ 342 ጨዋታዎች የሚካሄዱ ይሆናል።