ፈረሰኞቹ የቀድሞ ተጫዋቻቸው አስፈረሙ

የዓብስራ ሙልጌታ ከአራት ዓመታት በኋላ ወደ አሳዳጊ ቡድኑ ተመልሷል።


በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የቀድሞ ተጫዋቾቻቸው የዓብስራ ሙልጌታን አስፈረሙ። በክለቡ ታዳጊና ዋና ቡድን ከተጫወተ በኋላ በ2013 አሳዳጊ ክለቡን ለቆ ለጅማ አባጅፋር እና መቻል እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለሻሸመኔ ከተማ መጫወት የቻለው ይህ የመሀል ተከላካይ ባለፈው የውድድር ዓመት በሀያ ሰባት ጨዋታዎች ተሳትፎ 2430′ ደቂቃዎች ቡድኑን አገልግሏል።


ተከላካዩ ከወጣት እስከ ዋናው ቡድን ድረስ በመጫወት እግርኳስን ወደ ጀመረበት ክለብ ለመመለስ ፌርማውን ማኖሩ ተከትሎ ከአራት ዓመታት በኋላ ድግም በቅዱስ ጊዮርጊስ ማልያ የምንመለከተው ይሆናል።