አዞዎቹ ቶጎዋዊ የግብ ዘብ ለማስፈረም ተስማሙ

አርባምንጭ ከተማ ቶጓዋዊ ግብጠባቂ ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሰዋል።

የተጫዋቾች ውል በማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው በመቀላቀል ስብስባቸው በማጠናከር ላይ የሚገኙት አርባምንጭ ከተማዎች አሁን ደግሞ ቶጓዋዊ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል ፤ አዞዎቹን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ኢድሪሳ ኦጎጆ ነው።

ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት ኢንተንቴ ከተባለ የሀገሩ ክለብ ጋር ቆይታ የነበረውና ከዚህ ቀደም ለቶጎ የእድሜ ዕርከን ብሔራዊ ቡድኖች እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የዋናው ብሄራዊ ቡድን የግብ ዘብ የሆነው ይህ ተጫዋች ከክለቡ ጋር የነበረውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ በስፋት በሳውዲ ዓረብያ ሁለተኛ የሊግ እርከን ከሚወዳደረው ቢሻ ከተሰኘው ክለብ ጋር በስፋት ቢያያዝም በመጨረሻም ማረፍያው የኢትዮጵያው ክለብ ሆኗል።