ፈረሰኞቹ ሁለገቡን ተጫዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል

ባለፉት ዓመታት በሀምበሪቾ ቆይታ ያደረገው የመስመር አጥቂ ማረፊያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመሆን ተቃርቧል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ፈረሰኞቹ ወደ ዝውውሩ በመግባት ፍፁም ጥላሁን፣ ፀጋ ከድር ፣ የዓብስራ ሙልጌታ እና ጳውሎስ ከንቲባን ወደ ቡድናቸው መቀላቀላቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ የመስመር አጥቂ ሆነ የመስመር ተከላካይ በመሆን መጫወት የሚችለውን ቶሎሳ ንጉሴን ለማስፈረም መቃረባቸውን ሰምተናል ፤ ከዚህ ቀደም በቡራዩ ከተማ እና ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት ደግሞ በሀምበሪቾ ቆይታ ያደረገው ሁለገቡ ተጫዋች ቶሎሳ ንጉሴ የፈረሰኞቹ አምስተኛ ፈራሚ ለመሆን ተቃርቧል።

ተጨማሪ ተጫዋቾቸን ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በተለይ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው ለማስገባት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።