ኢትዮጵያ ቡና ናይጄሪያዊ አማካይ አስፈርሟል

ኢትዮጵያ ቡና የናይጄሪያ ዜግነት ያለውን አማካይ የግሉ አድርጓል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቀደም በማለት የጀመሩት እና የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ከኬኒያ ፓሊስ ጋር ከሜዳ ውጪ አድርገው ያለ ጎል ነጥብ ተጋርተው የተመለሱት ኢትዮጵያ ቡናዎች ሀብታሙ አሸናፊ ፣ ኦካይ ጁል ፣ እስራኤል ሸጎሌ ፣ ዳዊት ሽፈራው እና ጋናዊውን የግብ ዘብ ኢብራሂም ዳንላንድን በማስፈረም የስብሰባቸው አካል ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ናይጄሪያዊውን የ22 ዓመት የአጥቂ አማካይ ዲቫይን ናዋቹኩን በሁለት ዓመት ውል አስፈርመዋል።

በሀገሩ አዶሬሽን እና በንድል ኢንሹራንስ በተባሉ ቡድኖች ውስጥ የተጫወተው አማካዩ ቀጣዩ መዳረሻው የሀገራችን ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።