የባንክ እና ቪላ ጨዋታ በግብፅ አልቢትሮች ይመራል

የፊታችን ቅዳሜ በመዲናችን የሚደረገው የባንክ እና የዩጋንዳው ክለብ ቪላ ጨዋታ በግብፃዊ አልቢትሮች እንደሚመራ ታውቋል።

የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ የአህጉራችን ክፍሎች ሲደረጉ የነበረ ሲሆን የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም የመጀመሪያ ጨዋታውን ወደ ዩጋንዳ በማምራት ቪላን 2ለ1 በማሸነፍ የከወነ ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ 9 ሰዓት ያደርጋል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚደረገው የሁለቱ ቡድኖችን ጨዋታ ደግሞ አራት ግብፃዊያን አልቢትሮች እንደሚመሩት ታውቋል። በዚህም አህመድ ኤልጋንዶር በመሐል ዳኝነት ሙሐመድ አቡዚድ ሀልሀል እና አብድልፈታ መሀሙድ ኤልሳዲዲ በረዳትነት እንዲሁም አድል ኤልሴድ ሁሴን በአራተኛ ዳኝነት እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።