የቡና እና የኬኒያ ፖሊስን ጨዋታ የሚመሩ አልቢትሮች ታውቀዋል

እሁድ የሚደረገውን የኢትዮጵያ ቡና እና ኬኒያ ፖሊስ ጨዋታ የሚመሩት አልቢትሮች ታውቀዋል።

ሁለተኛው የካፍ የክለቦች አህጉራዊ የውድድር መድረክ በሆነው የኮንፌዴሬሽን ካፕ ፍልሚያ የቅድመ ማጣሪያ ላይ የሚገኘው የ2016 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ኢትዮጵያ ቡና ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ወደ ኬኒያ በማምራት የኬኒያ አቻውን ገጥሞ ያለ ግብ መለያየቱ አይዘነጋም። የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ የፊታችን ዕሁድ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ጨዋታውንም ከደቡብ የአህጉራችን ክፍል የመጡ አልቢትሮች እንደሚመሩት ታውቋል።

ጨዋታውንም የናሚቢያ ዜግነት ያላቸው ምዌሺሳማ ንጎንጎ ናፍታል በመሀል አልቢትርነት ሙዚቡዋኔ ሉምፖናኒ እና ማቲው ካኒያንጋ በረዳትነት እንዲሁም ሳሙኤል ማየሌ ንጊፓንዱልዋ በአራተኛ ዳኝነት በጋራ ይመሩታል።