ኢትዮጵያ ቡና ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬው ኢትዮጵያ ቡና የጋና ዜግነት ያለውን አጥቂ ወደ ስብስቡ አካትቷል።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታን ከኬኒያ ፓሊስ ጋር የሚያደረገው ኢትዮጵያ ቡና ለ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው ተጠናክሮ ለመቅረብ ይረዳው ዘንድ በክለቡ ከነበረው ኡጋንዳዊ ተከላካይ ዋሳዋ ጂኦፍሪ ፣ ከጋናዊው ግብ ጠባቂ ኢብራሂም ዳላንድ እና ከናይጄሪያዊው አማካይ ዲቫይን ናዋቹኩ በመቀጠል አራተኛው የውጪ ዜጋ ፈራሚ ጋናዊው የ25 ዓመት አጥቂ ሀፊዝ ኮንኮኒ ሆኗል።

አንድ ሜትር ከሰማኒያ አምስት ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው ይህ ጋናዊ አጥቂ ለሀገሩ ክለብ ቤቸም ፣ ለሳይፐርስ ክለብ ለሆኑት መርት አይሳክ ፣ ባፋ ሁሉኩ ፣ ለሊቢያው አል ኦሎምፒክ እና ለታንዛኒያው ያንጋ አፍሪካ ከተጫወተ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው በሁለት ዓመት ውል የሀገራቸን ክለብ  ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።