ምንተስኖት አዳነ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል

ከመቻል ጋር በስምምነት የተለያየው የተከላካይ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሌላኛውን የፕሪምየር ሊግ ክለብ ተቀላቅሏል።

በአሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ መሪነት በአዳማ ከተማ ለ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየከወኑ የሚገኙት ኢትዮጵያ መድኖች በዝውውሩ እስከ አሁን ጥቂት ዝውውሮችን የፈፀሙ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ባለ ልምዱን የተከላካይ እና የአማካይ ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነውን ምንተስኖት አዳነን በይፋ አስፈርመዋል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ረዘም ላሉ ዓመታት በክለቡ ዋናው ቡድን እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ተጫዋቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በርካታ ክብሮችን ካሳካ በኋላ በአዳማ ከተማ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ከመቻል ጋር ቆይታ የነበረው ሲሆን ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው ከመቻል ጋር በመለያየት ቀጣይ ክለቡ ኢትዮጵያ መድን ሆኗል።