ከፍተኛ ሊግ | ደሴ ከተማ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

በከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ የሆነው ደሴ ከተማ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል።

ደሴ ከተማ በአሰልጣኝ ዳዊት ታደለ እየተመራ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ “ለ” በመደልደል አርባ አምስት ነጥብ በመያዝ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል። ዘንድሮ በተሻለ ተጠናክሮ ለመቅረብ አሰልጣኙን ለተጨማሪ አንድ  ዓመት ለማቆየት መስማማቱን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

አሰልጣኝ ዳዊት በአሰልጣኝነት ሕይወቱ ከዚህ ቀደም የአዳማ ከተማን ወጣት ቡድን እንዲሁም ደግሞ ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ፣ አቃቂ ቃሊቲን እና ገላን ከተማን በማሰልጠን ያሳለፈ ሲሆን ዘንድሮ ደሴ ከተማን በመረከብ ቡድኑን ጠንካራ ተፎካካሪ ማድረጉ ይታወቃል።

አሰልጣኝ ዳዊት በቀጣይ ወደ ተጫዋቾች ዝውውር በመግባት ቡድኑን ለማጠናከር የተለያዩ ሥራዎችን ይሠራል ተብሎ ይጠበቃል።