ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር አንድ ተጫዋች አይጓዝም

ከደቂቃዎች በኋላ ወደ ታንዛኒያ በሚያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ አንድ ተጫዋች ከቡድኑ ጋር እንደማይጓዝ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።


በያዝነው ሳምንት በአረት ቀን ልዮነት ለሚያደርጋቸው ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ያለፉትን አስራ አምስት ቀናት ሲዘጋጅ የቆየው ብሔራዊ ቡድናችን ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ ዳሬ ሰላም የሚያቀና ይሆናል።

23 ተጫዋቾችን በመያዝ ወደ ስፍራው እንደሚያቀና በሚጠበቀው የዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ አንድ ተጫዋች እንደማይጓዝ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል። ተጫዋቹ ተከላካይ ፍሬዘር ካሳ ሲሆን የቀረበት ምክንያት ከፓስፖርት ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ሰምተናል።

ብሔራዊ ቡድናችን የመጀመርያ ጨዋታውን ከታንዛንያ ጋር ነሐሴ 29 ቀን ፣ ሁለተኛ ጨዋታውን ደግሞ ጳጉሜ 4 ቀን ከኮንጎ ዲ.ሪ ጋር ዳሬ ሰላም ብሔራዊ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።