ደሴ ከተማ ቡድኑን ማጠናከ ቀጥሎበታል

ደሴ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋቾች ስያስፈርም የነባሮቹን ውልም አድሷል።

አስቀድመው የዋና አሰልጣኛቸውን ዳዊት ታደለን ጨምሮ የወንድማማቾቹን አቡሽ ፀጋዬ እና ፀጋ ደርቤን ውል በማራዘመ ትግስቱ አበራ፣ ወጋየሁ ቡርቃ፣ ግብጠባቂው ይስሐቅ ተገኝ ፣ ጌታሰጠኝ ሸዋ እና ጆርጅ ደስታ ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉት ደሴ ከተማዎች አሁንም የነባሮች ውል በማደስ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድናቸው ማካተታቸውን ቀጥለውበታል።

ቡድኑ ባለፈው የውድድር ዓመት በክለቡ ቆይታ የነበራቸው ብሩክ ቦጋለ፣ ታፈሰ ሰርካ እና ዘሪሁን አብይ ውል ሲያድስ ባለፈው የውድድር ዓመት ከየካ ክፍለ ከተማ ጋር ቆይታ የነበረው አማካዩ ብስራት ታምራት፣ ተከላካይ ሞገስ ኩምቻ ከጋሞ ጨንቻ እንዲሁም ባለፈው የውድድር ዓመት በነቀምቴ ከተማ ቆይታው በከፍተኛ ሊጉ አስራ አንድ ግቦች ያስቆጠረው የቀድሞ የለገጣፎ ለገዳዲ አጥቂ ኢብሳ በፍቃዱ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ሆነዋል።