ሁለቱ የዋልያዎቹ ጨዋታዎች በቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋሉ

ታንዛኒያ ላይ የሚደረጉት ሁለቱ የዋልያዎቹ ጨዋታዎች የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኙ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በአሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሞሮኮ አዘጋጅነት በሚከናወነው የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ከታንዛንያ ጋር ነሐሴ 29 እንዲሁም ከኮንጎ ዲሪ. ጋር ጳጉሜ 4 ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎችን ለመከወን ወደ ዳሬሰላም ዛሬ አቅንቷል።

ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ከፊቱ ከባድ ፈተና የሚጠብቀው ቡድኑ የፊታችን ረቡዕ እና ሰኞ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እንደሚያገኙ የዝግጅት ክፍላችን አረጋግጣለች። በዚህም የሀገራችን ብሔራዊ ጣቢያ የሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመዝናኛ ቻነል አማራጩ ሁለቱንም ጨዋታዎች ለማስተላለፍ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል።