የነገውን የዋልያዎቹ ጨዋታ የሚመሩ አልቢትሮች ታውቀዋል

ነገ ምሽት 1 ሰዓት በታንዛኒያ እና ኢትዮጵያ መካከል የሚደረገውን ወሳኝ ጨዋታ የምዕራብ አፍሪካ አልቢትሮች ይመሩታል።

የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ለማድረግ በምድብ 8 ከታንዛኒያ፣ ጊኒ እና ከኮንጎ ዲሪ. ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎቹን ነገ ከታንዛኒያ ጋር እንዲሁን ሰኞ ከኮንጎ ዲሪ. ጋር ዳሬ ሰላም ላይ ያከናውናል።

በትናንትናው ዕለት ወደ ስፍራው ያቀናው ዋልያው ነገ ከሜዳው ውጪ በዳሬ ሰላም ብሔራዊ ስታዲየም የሚያደርገውን የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ሴኔጋላዊ አልቢትሮች እንደሚመሩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በዚህም ጨዋታውን በመሐል አልቢትርነት ኢሳ ሲ ሲመሩት ጂብሪል ካማራ እና ኖሀ ባንጉራ በረዳትነት እንዲሁም ኤል ሀጂ አማዱ ሲ በአራተኛ ዳኝነት ግልጋሎት እንደሚሰጡ ታውቋል።

ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ሲከናወን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ ለአድማጭ ተመልካቾች ፍልሚያውን እንደሚያስተላልፍ በትናንትናው ዕለት ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።