ሀዋሳ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል

በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመሩት ሀዋሳ ከተማዎች የሁለት ነባሮችን ውል አድሰዋል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሠሩና የሚገኙት በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመሩት ሀዋሳ ከተማዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቢኒያም በላይ ፣ ወንድማገኝ ማዕረግ ፣ ወንድማገኝ ኃይሉ ፣ ዮሴፍ ታረቀኝ እና ሰይድ ሀብታሙን ሲያስፈርሙ የእስራኤል እሸቱ እና ምንተስኖት ጊምቦን ውል ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት ማደሳቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ቡድኑ የሁለት ነባሮችን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።

ከሀዋሳ ወጣት ቡድን ተገኝቶ በኢትዮጵያ መድን እና በባህር ዳር ከተማ ተጫውቶ ወደ ልጅነት ክለቡ ሀዋሳ ተመልሶ ሲያገለግል የነበረው የመሐል ተከላካዩ ሠለሞን ወዴሳ እና ከታችኛው ቡድን አድጎ ስድስት ዓመታትን በዋናው ቡድን ያሳለፈው የተከላካይ አማካዩ ዳዊት ታደሠን ውል ነው ክለቡ ማራዘም የቻለው።