ዐፄዎቹ የግራ መስመር ተጫዋች ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል

የአሰልጣኝ ውበቱ አባተው ፋሲል ከነማ የግራ መስመር ተከላካዩን ወደ ስብስቡ አካትቷል።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት እና በለቀቋቸው ተጫዋቾች ምትክ አዳዲስ ተጫዋቾችን በመቀላቀል ከነባሮቹ ጋር በማጣመር በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሲሠሩ የነበሩት ፋሲል ከነማዎች ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ቡድናቸው አካትተዋል።

የግራ መስመር ተከላካዩ ተካልኝ ደጀኔ ወደ ቡድኑ ስብስብ የተካተተው አዲሱ ፈራሚ ሆኗል። የቀድሞው የደደቢት ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና አርባምንጭ ከተማ ተጫዋች የትውልድ ሀገሩን ክለብ ከለቀቀ በኋላ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከኢትዮጵያ መድን ጋር አሳልፎ ወደ ዐፄዎች ቤት አምርቷል።