ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚወዳደረው ሀላባ ከተማ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር ፈፅሟል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ዘለግ ያለ ተሳትፎ ያላቸው ሀላባ ከተማዎች ያለፈውን የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር ሲመሩ ቆይተው በምድብ አንድ በመደልደል በደረጃ ሰንጠረዡ በ38 ነጥቦች 7ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ የቻሉ ሲሆን ለቀጣዩ የ2017 የውድድር ዘመን ደግሞ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር መፈፀማቸውን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መረጃ አመላክቷል።

የክለቡ አዲስ አሰልጣኝ በመሆን የተሾመው መሐመድ ኑርንማ ነው። ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣት ቡድን የክለብ የስልጠና ሕይወትን የጀመረው እና በመቀጠል ደግሞ በኮልፌ ቀራኒዮ እና ያለፉትን ሁለት ዓመት ከግማሽ ደግሞ በቤንች ማጂ ቡና እስከተጠናቀቀው ዓመት አጋማሽ ካሳለፈ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው የበርበሬዎቹ ቤት ሆኗል።