ሀዲያ ሆሳዕና የአጥቂ አማካይ ለማስፈረም ተስማምቷል

ነብሮቹ የማሊ ዜግነት ያለውን ተጫዋች በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስባቸው ለማካተት እጅግ ተቃርበዋል።

በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ መሪነት በክለቡ መቀመጫ ከተማ በርከት ያሉ ያስፈረሟቸውን ተጫዋቾች ከነባሮቹ ጋር በመቀላቀል የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየከወኑ በወዳጅነት ጨዋታዎችም ራሳቸውን ሲፈትሹ የሰነበቱት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ማሊያዊ ዜግነት ያለውን ሴኮ ኮናቴን በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስባቸው ለመቀላቀል መስማማታቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ የደረሳት መረጃ አመላክቷል።

አንድ ሜትር ከሰማንያ አንድ ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው እና ለሀገሩ ክለቦች ስታድ ማሊን እና ላፊያ ከተጫወተ በኋላ ወደ አልጄሪያው ዩኤስ ኤም አልጀርስ በማምራት የአንድ ዓመት ቆይታን ያደረገው አማካዩ ከቡድኑ ጋር ከተለያየ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው በአንድ ዓመት ውል የሀገራችን ክለብ የሆነው ሀዲያ ሆሳዕና ሊሆን እጅግ ተቃርቧል።