ብርቱካናማዎቹ አምበሎቻቸውን አሳውቀዋል

ድሬደዋ ከተማ ለዘንድሮ የውድድር ዓመት ቡድኑን በአምበልነት እንዲመሩ አራት ተጫዋቾችን መሰየማቸው ታውቋል።

በዝውውሩ መስኮቱ በስፋት በመሳተፍ አላዛር መርኔ፣ አስራት ቱንጆ፣ አህመድ ረሺድ፣ አብዱልሰላም የሱፍ፣ መሐመድኑር ናስር፣ አቡበከር ሻሚል፣ መስዑድ መሐመድ፣ ጀሚል ያዕቆብን ከማስፈረም ባለፈ በርከት ያሉ የወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም በአዳማ ከተማ ዝግጅታቸውን ሲያደርጉ የከረሙት ድሬዎች በአሁኑ ደግሞ ወደ መቀመጫ ከተማቸው ተመልሰዋል።

ቡድኑ ከነባር አምበሎቹ ጋር እንደመለያየቱ እና በአዲስ አሰልጣኝ የሚመራ መሆኑን ተከትሎ በ2017 የውድድር ዘመን የቡድኑ አዲስ አምበሎች እነማናቸው የሚለውን ጉዳይ ተጠባቂ ነበር ፤ ሶከር ኢትዮጵያ ባደረገችው ማጣራት ቡድኑን በአንበልነት እንዲመሩ የተመረጡትን አራት አምበሎች አውቃለች።

ቀዳሚው የቡርትካናማዎቹ አንበል በመሆን የተመረጠው አማካዩ መስዑድ መሐመድ ነው። ባለብዙ ልምዱ ይህ አማካኝ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ፣ በኢትዮጵያ ቡና፣ በጅማ አባ ጅፋር ፣ በአዳማ ከተማ አምበል ሆኖ ከመምራቱ ባሻገር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአምበል እንደነበረ ሲታወቅ አሁን ደግሞ የአዲሱ ክለቡ ቀዳሚ ተመራጭ ሆኗል።


ሁለተኛ ተመራጭ አንበል እንዲሆን የተሰየመው
የታዳጊ ቡድን ፍሬ የሆነው እና ዘንድሮ ውሉን ያራዘመው አማካይ ያሬድ ታደሰ ሲሆን በሦስተኝነት ደግሞ ዘንድሮ ቡድኑን የተቀላቀለው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ጀሚል ያዕቆብ ሲመረጥ የቡድኑ አራተኛ አምበል ሆኖ የተመረጠው ደግሞ ከድሬደዋ ከተማ ማሊያ ውጭ ሌላ መለያ ለብሶ የማያቀው እና ያለፉትን አራት አመታት ቡድኑን ያገለገለው እና ዘንድሮ ውሉን ያራዘመው አቤል አሰበ በመሆን መመረጣቸው ታውቋል።