ሀዲያ ሆሳዕና የቀድሞ ግብ ጠባቂውን የግሉ አድርጓል

ነብሮቹ ሁለት የቀድሞ ግብ ጠባቂዎችን ከተመለከቱ በኋላ በመጨረሻም አንዱን የስብስባቸው አካል አድርገዋል።

በዝውውሩ ላይ ዘግየት ያለን ተሳትፎ ማድረግ የቻሉት እና ቀስ በቀስ ቡድናቸውን ማጠናከር የቻሉት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ለቀናት ለሁለት ግብ ጠባቂዎች የሰጡትን የሙከራ ጊዜ ተከትሎ በመጨረሻም የቀድሞ ግብ ጠባቂያቸው የሆነውን ስንታየሁ ታምራትን ወደ ስብስባቸው አካትተውታል።

ከደደቢት ተስፋ ቡድን ከተገኘ በኋላ ከዚህ ቀድም ለሀዲያ ሆሳዕና እንዲሁም በአንደኛ ሊግ ከዚህ ቀደም ለተሳተፈው ሀዲያ ሌሙ ፤ በከፍተኛ ሊጎቹ ሀላባ እና ወልዲያ ቆይታ የነበረው የግብ ዘቡ ወደ ቀደመ ክለቡ መመለሱን ክለቡ አሳውቆናል።