ሀዲያ ሆሳዕና አራቱን አምበሎች አሳውቋል

በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀዲያ ሆሳዕናን በአምበልነት የሚያገለግሉ አራት ተጫዋቾችን ክለቡ አሳውቆናል።

በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ መሪነት በክለቡ የነበሩ ተጫዋቾችን ኮንትራት ያራዘሙት እና እንደ ኢዮብ ዓለማየሁ ፣ በረከት ወንድሙ ፣ ጫላ ተሺታ ፣ ብሩክ በየነ ፣ ሳማኪ ሚካኤል እና በትናንትናው ዕለት ደግሞ ሴኮ ኮናቴን የግላቸው ለማድረግ የተስማሙት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ለ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሲሠሩ ቆይተው ውድድሩ ወደሚዘጋጅበት ድሬዳዋ ከተማ ከማምራታቸው በፊት ቡድኑን በአምበልነት የሚመሩ ተጫዋቾችን ዝርዝር ለዝግጅት ክፍላችን አሳውቀዋል።

እንደ ክለቡ መረጃ ከሆነ ቡድኑን በተከታታይ ዓመታት በአምበልነት እየመራ የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ሄኖክ አርፊጮን በዋና እንዲሁም ተከላካዮቹ በረከት ወልደዮሐንስ እና ዳግም ንጉሤ ሁለተኛ እና ሦስተኛ እንዲሁም ደግሞ ሁለገቡ ተጫዋች ሳሙኤል ዮሐንስ አራተኛ አምበል ሆነው እንዲመሩ ተመርጠዋል።