ሀዋሳ ከተማ ተጨማሪ ረዳት አሰልጣኝ ሾሟል

አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ተጨማሪ ረዳት አሰልጣኝ ወደ አሰልጣኝ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።


ለአዲሱ የውድድር ዘመን አዳዲስ ወደ ክለቡ ያመጧቸውን ተጫዋቾች ከነባሮች በጋራ በማጣመር የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው ሲከውኑ የከረሙት ሀዋሳ ከተማዎች ሊጉ ወደ ሚደረግበት ድሬዳዋ ከተማ በነገው ዕለት ከማምራታቸው ቀድም ብለው በትላንትናው ዕለት በክለቡ ከነበሩት ረዳት አሰልጣኙ ብርሀኑ ወርቁ እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ አዳሙ ኑሞሮ በተጨማሪ የአዲስ ረዳት አሰልጣኝ ሹመትን ፈፅመዋል።


ወንድማገኝ ተሾመ የክለቡ ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ በአሰልጣኝ ዘርዓይ የተመረጠው አሰልጣኝ ሆኗል። የቀድሞው የሲዳማ ቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና የግራ መስመር ተከላካይ የነበረው ወንድማገኝ ከእግር ኳስ ከተገለለ በኋላ አሰልጣኝነትን የሲዳማ ቡና የተስፋ ቡድንን በማሰልጠን ወደ ስልጠናው የገባ ሲሆን በመቀጠል የሲዳማ ቡና ረዳት እና ዋና አሰልጣኝ በመሆን ማገልገሉ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ የሐይቆቹ የረዳት አሰልጣኞች በመሆን የሚሰራ ይሆናል።