ቡናማዎቹ አምበሎቻቸውን አሳውቀዋል

በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ ቡና አምበል ሆነው የሚመሩ ሦስት ተጫዋቾችን ክለቡ አሳውቆናል።

በአሰልጣኝ ነጻነት ክብሬ እየተመሩ አዲሱን የውድድር ዓመት የሚጠባበቁት ኢትዮጵያ ቡናዎች ከኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ፣ ከኮንፌዴሬሽን የቅድመ ማጣርያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች እና አሜሪካ ላይ ከተደረገ የሸገር ደርቢ ጨዋታ በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ይመለሳሉ።

በርካታ ቁልፍ ተጫዋቾችን አጥቶ በወጣቶች የተገነባውን ቡድን ዘንድሮ በአምበልነት የሚመሩ ሦስት ተጫዋቾችን ደግሞ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። በዚህም መሠረት ከሀገሩ የእግርኳስ ሕይወቱን ጀምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በነበረባቸው ሁለት ዓመታት በአምበልነት የመራው ራምኬል ጀምስ የቡድኑ ተቀዳሚ አምበል ሆኖ ኢትዮጵያ ቡናን እንዲመራ ሲወሰን ዋሳዋ ጄኦፍሪ ሁለተኛ ፣ ስንታየሁ ዋለጬ ደግሞ ሦስተኛ አምበል ሆነው ተሰይመዋል።