ፈረሰኞቹ ቶጓዊ አጥቂ የግላቸው አድርገዋል

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የቶጎ ዜግነት ያለውን አጥቂ ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በመያዝ በቢሾፍቱ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን አገባደው ወደ ድሬዳዋ የሚያመሩት በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ቶጓዊ አጥቂ የስብስባቸው አካል አድርገዋል።

ቡድኑን የተቀላቀለው ቶጓዊው የ27 ዓመት አጥቂ ሴሚሆ ታቻታኮራ ነው። የሀገሩን ክለብ ኤ ኤስ ሲ ካራን በመልቀቅ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ክለብ ኤ ኤፍ ሲ ሉፓፓ ቆይታን ካደረገ በኋላ ቀጣይ መዳረሻው የፈረሰኞቹ ቤት ሆኗል።