የፋሲል ከነማ አምበሎች ታውቀዋል

ዐፄዎቹ ለ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአምበልነት የሚመሯቸውን ተጫዋቾች አሳውቀውናል።

በዛሬው ዕለት ምሽት 1 ሰዓት ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድራቸውን የሚጀምሩት ፋሲል ከነማዎች በአምበልነት የሚመሯቸውን ተጫዋቾች ይፋ አድርገዋል።

በዚህም የቀድሞ የደቡብ ፖሊስ ፣ ደደቢት ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም በፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ሕይወቱ ለደቡብ አፍሪካዎቹ ቢድቬስት ዊትዝ እና ፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ የተጫወተው እና በታኅሣሥ ወር 2015 ራሱን ከማግለሉ በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የነበረው ጌታነህ ከበደ ባለፈው የውድድር ዓመት የተቀላቀለውን ክለብ ለተከታታይ ሁለተኛ ዓመት በአምበልነት እንደሚመራ ሲታወቅ ምኞት ደበበ ሁለተኛ ፣ አቤል እያዩ ሦስተኛ እና አቤል እንዳለ ደግሞ አራተኛ አምበል ሆነው ተሰይመዋል።