ሄኖክ አዱኛ የግብፅ ዝውውሩን አጠናቋል።

የሊጉን ዋንጫ  ደጋግሞ ከፍ ማድረግ የቻለው የመስመር ተከላካዩ ወደ ግብፅ ሊግ የሚያደርገውን ዝውውር አጠናቋል።

ከሳምንታት በፊት የመስመር ተከላካዩ ሄኖክ አዱኛ በግብፁ ክለብ ሃራስ ኤል ሁዶድ እየተፈለገ እንደሆነ እና ዝውውሩን በቀጣዮቹ ቀናት ሊያጠናቅቅ እንደሚችል ዘግበንላችሁ ነበር።

ከትናንት በስቲያ ወደ ግብፅ ያቀናው ሄኖክ ዛሬ ለሁለት ዓመታት በሃራስ ኤል ሁዶድ ለመጫወት የተስማማበትን ፊርማ አኑሯል። ይህን ተከትሎ ሄኖክ አዱኛ ከጋቶች ፓኖም ቀጥሎ በክለቡ የተጫወተ ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሆኗል።

ከዚህ ቀደም ሄኖክ በሀላባ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ ተጫውቶ ከጅማ አባጅፋር ጋር የሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ  ያለፉትን ስድስት ዓመታት በስኬት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሁለት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ከፍ ማድረጉ ይታወቃል።