የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር የሚያደርጋቸው ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች የቦታ እና የቀን ለውጥ ተደርጎባቸዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸው ሦስተኛ እና አራተኛ የምድብ ጨዋታዎች ላይ የቀን እና የቦታ ለውጥ መደረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ እና የጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች በጋራ ለካፍ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በጨዋታዎቹ ላይ የቦታ እና የቀን ሽግሽግ የተደረገበት ሲሆን ሦስተኛው የምድብ ጨዋታ ጊኒ የሜዳዋ ጨዋታን ለማድረግ ያስመዘገበችው ያሞሱክሩ የሚገኘው ስታድ ኮናን ባኒ ወደ አቢጃኑ ስታድ ደ ኢቢምፔ ፤ የጨዋታው ቀን ደግሞ በአንድ ቀን ተራዝሞ ጥቅምት 2 ከምሽቱ 1፡00 ላይ የሚያከናውን ሲሆን አራተኛ የምድብ ጨዋታውን በተመሳሳይ ከጊኒ ጋር ጥቅምት 4 ሊደረግ የነበረው ጨዋታ በአንድ ቀን ተራዝሞ ወደ ጥቅምት 5 ተሸጋሽጓል። የቦታ እና የሰዓት ለውጥ ሳይደረግበትም አቢጃን የሚገኘው ስታድ ደ ኢቢምፔ ምሸት 4፡00 ላይ ያከናውናል።