ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጥቂ አስፈርሟል

በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገዱ የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀድሞው አጥቂውን ዳግም አግኝቷል።


በክረምቱ የዝውውር መስኮት ጥቂት ተሳትፎን ብቻ ማድረግ የቻለው በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ ባደረገው ብቸኛ ጨዋታው አርባምንጭ ከተማን በመርታት በድል ዓመቱን መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን ክለቡም ራሱን ለማጠናከር በትላንትናው ዕለት የቀድሞው ተጫዋቹን የግሉ አድርጓል።

በአጥቂ ስፍራ ላይ የሚጫወተው ሐይከን ድዋሙ ደግሞ የክለቡ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማደግ ባደረገው የ2015 የውድድር ዘመን በከፍተኛ ሊጉ ከክለቡ ላይ ቆይታ የነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ መድን እና የአምናው የሸገር ከተማ አጥቂ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ካሳለፈው የክረምት የልምምድ ቆይታ በኋላ በትላትናው ዕለት በመድን እና በባንክ አብረው መስራት ከቻሉት አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ጋር ዳግም የተገናኘበትን ዝውውር አጠናቋል።