ናትናኤል ዘለቀ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል

ከአስራ አራት ዓመታት ቆይታ በኋላ ከእናት ክለቡ ጋር በስምምነት የተለያየው አማካይ መዳረሻው ቢጫዎቹ ቤት ሆኗል።


በዛሬው ዕለት ናትናኤል ሰለሞንን ለማስፈረም የተስማሙት እና ቀደም ብለው በርከት ያሉ ዝውውሮች ያገባደዱት ቢጫዎቹ አሁን ደግሞ ላለፉት አስራ አራት ዓመታት ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን በፈረሰኞቹ ቆይታ የነበረው አማካዩ ናትናኤል ዘለቀን አስፈርመዋል።

ከፈረሰኞቹ ጋር ስኬታማ ዓመታት እና ስድስት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ማንሳት የቻለው ናትናኤል በክለብ ደረጃ ከቅዱስ ጊዮርጊስ መልያ ውጭ ለብሶ ያልተጫወተ ሲሆን አማካዩ ከእናት ክለቡ ጋር የአንድ ዓመት ውል እየቀረው በስምምነት ተለያይቶ ወደ ወልዋሎ አምርቷል።

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ ካደረጉ ክለቦች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት ወልዋሎዎች
ናትናኤል ዘለቀን የክረምቱ የመጨረሻ ፈራሚያቸው በማድረግ አገባደዋል።