የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሜቴ ወልቂጤ ከተማ ባስገባው የይግባኝ አቤቱታ ዙሪያ ውሳኔ አሳልፏል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የውድድር አመራር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ መስከረም 14 እና 19 2017 ይግባኝ ባይን አስመልክቶ ያሳለፈውን የዲሲፕሊን ውሳኔ ለማሻር የቀረበ የይግባኝ አቤቱታ በማለት የይግባኝ ጥያቄያቸውን አስገብተዋል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ሲያጣራ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ያስተላለፈውን ውሳኔ በቀን መስከረም 19 2017 ለክለቡ ማድረሱን ለማረጋገጥ ተችሏል ያለ ሲሆን ስለሆነም ተሻሽሎ በወጣው የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን መመሪያ አንቀጽ 98 መሠረት ክለቡ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ገደብ እና ግዴታዎችን ያላሟላ በመሆኑ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የሚከተለውን ውሳኔ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።
1ኛ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ በወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ክለብ ላይ የወሰነው ውሳኔ ክለቡ ያቀረበው አቤቱታ የይግባኝ ማስገቢያ ጊዜውን ያልጠበቀ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው አልተቀበለውም ስለሆነም ውሳኔው ጸንቷል።
2. ይግባኝ ባይ ለይግባኝ ያስያዘው ገንዘብ ለፌዴሬሽኑ ገቢ ሆኗል።