ከፍተኛ ሊግ | አዲስ አበባ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚካፈለው የመዲናይቱ ተወካይ የአዲስ አሰልጣኝ ሹመትን ፈፅሟል።


በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሁለት አጋጣሚዎች ተሳትፎን ያደረገው እና ላለፉት ዓመታት ደግሞ በከፍተኛ ሊጉ ላይ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ያለፈውን ዓመት በምድብ ሀ ስር ተደልድለው በ40 ነጥቦች በደረጃ ሰንጠረዡ ስድስተኛ ላይ ተቀምጠው ማጠናቀቅ ችለዋል።

አምና ቡድኑን በአሰልጣኝነት እየመሩ ከነበሩት አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጋር የተለያየው ቡድኑ በምትኩ አሰልጣኝ ጥላሁን ተሾመን ሾሟል።

የቀድሞው የለገጣፎ ለገዳዲ አሰልጣኝ ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊግ በማሳደግ በጥቂት ጨዋታዎች ክለቡን የመሩ ሲሆን የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ደግሞ በሸገር ከተማ ቆይታን ማድረግ ሲችሉ በአዲሱ የውድድር ዘመን ደግሞ በመዲናይቱ ክለብ የምንመለከታቸው ይሆናል።