የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚደረግባቸው ከተሞች ታውቀዋል

የ2017 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር  የሚደረጉባቸው ሁለት ከተሞች ይፋ ሆነዋል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚደረገው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2017 የውድድር ዘመን ከጥቅምት 16 ጀምሮ መከናወን እንደሚጀምር ይታወቃል። በሁለት ምድብ ተከፍሎ የሚደረገው የዘንድሮው የሀገሪቱ ሁለተኛ የሊግ ዕርከን ዛሬ ረፋዱን 3፡00 ጀምሮ ቦሌ በሚገኘው ዋሽንግተን ሆቴል የዕጣ ማውጣት መርሐግብር እየተደረገበት የሚገኝ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይም ውድድሩ በሁለት ከተሞች እንዲካሄድ መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ በስፍራው ተገኝታ ለማወቅ ችላለች።

በዚህም መሠረት ልክ እንዳለፈው ዓመት ሁሉ ውድድሮቹ በመዲናችን አዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተማ ላይ እንዲከናወኑ የተወሰነ ሲሆን በውድድሩ ላይ ደግሞ ሃያ አራት ቡድኖች እንደሚካፈሉ ለማወቅ ተችሏል።

በዕጣ ማውጣት መርሐግብሩ ላይ የሚነሱ አዳዲስ ሀሳቦችን በቀጣይ ጥንቅር ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።