አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ስለቀጣይ ዕቅዳቸው ሀሳብ ሰጥተዋል

ከ20 ዓመት በታች ውድድርን አስመልክቶ በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመረከብ ስለማሰባቸው ምን ተናገሩ?

በታንዛኒያ የነበረው ቆይታቸውን አስመልክቶ አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ በተለያዩ ጉዳዮች አስገራሚ አስተያየት እየሰጡ ይገኛል። “ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ትልልቅ አሰልጣኞች መካከል አንድ ብትጠሩ እኔ ነኝ፤ ሁለት ብትጠሩ እኔው ነኝ።” በማለት ያልተጠበቀ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ በቦታው በሚገኙ የስፖርት ጋዜጠኞች ጥያቄ ተነስቶባቸዋል። “ትልቅ አሰልጣኝ ነኝ ብለዋል፤ በቀጣይ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ የመሆን ዕቅድ አለዎት ወይ?” ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አሰልጣኞች አንድ ብትጠሩ እኔ ነኝ፤ሁለት ብትጠሩ እኔው ነኝ ስል በትምህርት ደረጃዬም ሆነ በተግባር እውቀቴ ባለኝ ከፍተኛ ልምድ ባስመዘገብኳቸው ውጤቶች ከፍታ እና ዝቅታ ቢኖርም እንዲሁም ሁሌም ራሴን በስልጠናው ለማሳደግ በየጊዜው የማሻሻያ ስልጠናዎችን በቅርቡ ስወስድ እንኳን እነርሱን መጠየቅ ይቻላል። ከሁሉም በተሻለ እንጂ ባነሰ ተሳትፎ አልነበረኝም ይሄን ሁሉም ይመሰክርልኛል። ስለዚህ ሁልጊዜ በሙያዬ የምችለውን ለማድረግ ካለኝ ጥረት አንፃር ተነስቼ ካሉት አሰልጣኞ እኔ ብቁ ነኝ እላለው። ከኢትዮጵያ አሰልጣኝ የሚመረጥ ከሆነ ለመወዳደር ዝግጁ ነኝ። ዕቅዴን አስገብቼ ለመስራት አስባለው።”

በቀጣይ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ስራ ይቀጥላሉ ወይስ? የተባሉት አሰልጣኝ ሥዩም ሲመልሱ “ ለዚህ ለሴካፋ ውድድር ብቻ ነው ኮንትራቴ የሚያገለግለው። ከዚህ ውጭ ብዙም ነገር የለም።” ብለዋል።