አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ስለታንዜኒያ ቆይታቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል

በሴካፋ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ተካፍሎ የተመለሰው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በውድድሩ ስለነበራቸው ተሳትፎ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አሰልጣኙ በመግቢያ ንግግራቸው ከምልመላ ጀምሮ ወደ ታዛኒያ እስኪያቀኑ ድረስ አስራ ሁለት የዝግጅት ቀናት የነበራቸው መሆኑ አንስትው ሆኖም ይሄ ግንዛቤ ተወሰደ አልተወሰደም በውድድሩ ላይ ለተመዘገበው ውጤት ሰፊውን ስፖርት አፍቃሪ ህዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ወደ ውድድሩ ቦታ ሲደርርሱም መሬት ላይ ወርዶ ያዩት ነገር እንደሚወራው የእኛ ልጆች ብቻ ዕድሜያቸው ከሰላሳ ዓመት በላይ እየተባለ እንደተነገረው ሳይሆን ውድድሩ ከ20 ዓመት በታች ሳይሆን የቻን ውድድር ይመሰል ነበርም ብለዋል።

ጉዳዩንም ይበልጥ ሲያብራሩ ሌሎች ተሳታፊዎች ያቀረቧቸው ተጫዋቾች ከእኛ ልጆች ተመጣጣኝ ወይም የሚበለጡ ናቸውም ብለዋል።

ሀገር ቤት ስለነበራቸው ዝግጅትም ሲያስረዱ አስራ አንድ ተጫዋችን ለማግኘት እንደተቸገሩ የገለፁ ሲሆን ባደረጓቸው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች ተጫዋቾች ለሊግ ውድድር ወደ ክለቦቻቸው በማምራታቸው መነሻነት የመጀመሪያ 11 ተጫዋቾቻቸውን ያገኙት ወደ ታንዛኒያ ካመሩ በኃላ መሆኑን አብራርተው ቡድናቸው ውጤታማ ባይሆንም ቡድናችን አንገት የሚያስደፋ ክብርን የሚያሳጣ እንቅስቃሴ አላደረገም ብለዋል።

በገለፃቸው የመጨረሻ ክፍልም ከ20 ዓመት በታች የሊግ ውድድር ላይ ራሱ በትክክል ከ20 ዓመት በታች የሆነ ተጫዋች የሉም ያሉ ሲሆን ” የማልክዳቹሁ ነገር ግን ልምዳቸው ይጠቅመናል ፓስፖርታቸው ይሆናል ብለን የተወሰኑ ተጫዋቾች ወጣ ያሉ ይዘን ሄደናል።” ሲሉም ተደምጠዋል።

በማስከተል ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን እኛም አንኳሮቹን በዚህ መልኩ አቅርበናቸዋል።

የተጫዋቾች ምርጫን በተመለከተ ?

“95% አሰልጣኝ አብይንም ሆነ አምሳሉን በምርጫው ውስጥ አካትቺያለው ፤ በእርግጥ ነው ልጆቹን አላውቃቸውም። ሁሉንም ተጫዋቾች ቁጭ ብለን ከዚህ በፊት የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ክፍል የመዘገባቸው ነበሩ እርሱንም ይዘን የእኛንም ጨምቀን ነው ምርጫውን ያደረግነው። አጠቃላይ ተናበን ጊዜ ሰጥተን ያደረግነው ምርጫ ነው።”

ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ውድድር ተጫዋቾች ያልተመረጡበት ምክንያት ?

“አዎ ከ20 ዓመት በታች ውድደር ተጫዋቾች አልመረጥንም ፤ ለምን እነዚህ የመረጥናቸው ተጫዋቾች ይሻላሉ ብለን ነው። እነዚህ የተመረጡ ልጆች ከ2015 ጀምሮ ከቢ ቡድን አንስቶ ተስፋ ቡድን ተጫውተው ወደ ዋናው ቡድን አድገው ወጣ ገባ የሚሉ ቋሚነት ያላገኙ ናቸው። ከረዳቶቼ ጋር በጥልቀት ተነጋግረን እነዛን ጨምቀን ይዘን ሄደናል። በሴካፋ ውድድር ላይ በሀገራችን ከሚካሄደው ከ20 ዓመታ በታች ከሚጫወቱ ብቻ ይመረጥ የሚል የተገደበ ህግ ቢኖር ኖሮ ሙሉውን ከዚያ አድርገን መርጠን እንሄድ ነበር። ግን የነበረው ነገር ክፍት የነበረ ስለሆነ ከፕሪሚየር ሊጉ፣ ከፍተኛ ሊጉ ላይ ከሚጫወቱ ፓስፖርታቸው ለመጫወት የሚፈቅድላቸው ካሉ እነርሱ እንድናካትት ስለሚፈቅድልን ይህንን አድርገናል።”

ከውጪ የመጡ ተጫዋቾች ሲቀነሱ የዓየር ንብረቱን ለመላመድ ጊዜ የላቸውም በሚል እንደነበር ተጠቅሶ ነበር። የተመረጡ ተጫዋቾችስ የታንዛኒያን ለመልመድ አልተቸገሩም ? በወሰድኳቸው ብለህ የተፀፀትከው ነገር አለ ?

“ከውጭ በመጡ ተጫዋቾች በተመለከተ ላጥራላቹሁ ወደ እዚህ የመጡ ልጆች ስድስት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሳምንት ቀድሞ የመጣው ይበልጣል ከስፔን ነው። የቀሩት አምስት ተጫዋቾች የመጨረሻው ሰዓት ላይ ነው የደረሱት በዚያ ጊዜ ውስጥ ቀልቤን የሳቡኝ እኔን ብቻ ሳይሆን አብረውኝ ያሉት ረዳቶች ጭም በብቃታቸው ያመንባቸው ለነገ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ይሆናሉ ያልኳቸው አእላፍ አያሌው አጥቂው እና ናትናኤል የግራ መስመር ተከላካዩ ናቸው። እነዚህ ልጆች ካላቸው አቅም አንፃር በብሔራዊ ቡድን ቢካተቱ የሚል አሁንም ውስጤ አለ የተቀሩት ግን እዚህ ሀገር ካሉት ልጆች የተሻሉ አይደሉም። ይፀፀትሀል ለተባለው ከላይ ባለው መልኩ የመለስኩት ይመስለኛል።”

አጥቅቶ የሚጫወት ቡድን እገነባለው ብለህ ነበር። ነገር ግን 8 ጎል ተቆጥሮባችሁ 3 ብቻ ከማስቆጠራችሁ አንጻር በማጥቃት እንቅስቃሴው የጎደለን ነገር ምንድን ነው ብለህ ታስባለህ ?

“እንደ ቡድን ለምሳሌ ሦስት ለዜሮ የተሸነፍንበት የዩጋንዳ ጨዋታ የተሻለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ትርጉም ባለው መልኩ ማለት ነው። የጎል ዕድሎች ሁለትም ሦስትም አግኝተናል። በውሳኔ ችግሮች ጋር ተያይዞ ጎል ማስቆጠር ነው ያልቻሉት። ይህ የክለብ ልምዳቸው የኖሩበት ጊዜ ነው። ያገኘናቸውን ዕድሎች ጎል ሆነው ቢቆጠሩ የሚፈጥረው መነቃቃት ቀላል አልነበረም። በአጠቃላይ እነዚህ ነገሮች ላይ በቀጣይ ትኩረት አድርጎ መስራት የጨዋታ ልምዱን እያገኙ ሲመጡ የተሻለ ነገር ይመጣል ብዬ አስባለው።”