አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ስለአጨዋወት መንገዳቸው ምን አሉ?

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ከጊኒው የደርሶ መልስ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ በኋላ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የመሰብሰብያ አዳራሽ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማቅረባችን ይታወሳል አሁን ደግሞ አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በአህጉራዊ ጨዋታዎች በክለብም ሆነ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ የተከተሉት አጨዋወትን ለመፈተሽ ሞክረዋል ወይ ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ የሰጡት ምላሽ እንደሚከተለው ቀርቧል።

“በክለብ ደረጃ ውጤታማ አይደሉም ከዚህ በላይ መሄድ ይቻል ነበር ወይ የሚታወቅ ነው፤ አንድ ገብረመድህን አንድ ክለብ ወይም ብሄራዊ ቡድንን በአንድ ሰሞን መቀየር አይችልም፤ ይሄ መታወቅ አለበት። አጨዋወት መንገድህ ለምን አትቀይርም ለሚለው አሁንም ቢሆን አልቀይርም፤ ቀጥተኛ አጨዋወት ነው የምጫወተው። ሀያ አምስት ዓመት ክለቦችን ሳሰለጥን ውጤታማ የሆንኩበት አጨዋወት ነው። ባንክን ሳሰለጥን አልፈናል እኮ ደደቢትንም ሳሰለጥን ሜዳቸው ላይ አራት ለአራት ወጥተን በሜዳችን ሁለት ለባዶ በማሸነፍ አልፈናል ይሄ እንደ ውጤት የማይገለፅ ከሆነ የራስህ አገላለፅ ነው።  እንደ አጠቃላይ ግን እኔ የራሴ የሆነ አጨዋወት አለኝ፤ ኳስ የመቆጣጠር አቅም ያለው ቡድን መገንባት አንድ ነገር ነው፤ ግን ደሞ ወደ ፊት ያተኮረ መሆን አለበት ነው የኔ ሃሳብ። ቀጥተኛ የሆነ አጨዋወት መጫወት አለበት። ቅብብሎች ላይ ብዙም አላተኩርም አሁንም ቢሆን። በፍጥነት መድረስ እንዲችሉ ነው ፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ደግሞ ይሄ ብዙ ነገር ይፈልጋል፤ ብዙ አቅም ይፈልጋል። እንደ ሀገር ያለን ተጨባጭ ሁኔታ ማገናዘብ ያለብን ይመስለኛል።”

የአጨዋወት ስልቴን አልቀየርም ብለዋል ያንን መንገድ ተጠቅመው ውጤት እያመጡ አይደለምና ውጤት ካልመጣ ለምንድነው የጨዋታ ፍልስፍናችሁን ማትቀይሩት?

”የእኔ እምነት ነው።እስከአሁንም የመጣውበት ነው።የአጨዋወት ዘይቤ የራስህ የሆነ አጨዋወት ይኖርሃል።አሁን እኔ እያልኩ ያለውት በቀጥተኛ ጨዋታ በመጫወታችን ብቻ አይደለም እየተሸነፍን ያለነው አሁን መታወቅ ያለበት ማለት ነው።ያልሆኑ ስህተቶች ስላሉ ነው።በርግጠኝነት ኳሱን ብንይዝ ቀኑን ሙሉ ብንይዝም ዞሮ ዞሮ ማሸነፋቸው አይቀርም መሸነፋችን አይቀርም ፣ከእዛም በላይ ሊሆን ይችላል።ስላልሆነ ብቻ አታንሱ።ይሄ የእኔ እምነት ነው።ለምሳሌ ልንገራችሁ ቀጥተኛ አጨዋወት ነው ምጫወተው በዚህ ፍጥነት በዚህ ሁኔታ ጎል ውስጥ ይገባሉ ወይ እስከዛሬ? ተጫዋቾቹ ሳጥን ውስጥ ሙከራ አድርገው ያውቃሉ ወይ?ጎል አናገባም አሁን ብዙ ጎል እየሳትን ነው።ስራ መስራት ያስፈልጋል ልክ ነው።ግን በእምነት ደረጃ ይሄ ወደፊት ቶሎ ቶሎ እንዲደርስ ለማድረግ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል።” ሲሉም ተደምጠዋል።