ከፍተኛ ሊግ | አዲስ አዳጊው ሱሉልታ ክፍለ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ “ለ” ተወዳዳሪው ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ራሱን አጠናክሯል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ከታችኛው ከአንደኛ ሊጉ በማደግ ከሚካፈሉ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ሱሉልታ ከተማ በ2017 የውድድር ዘመን በምድብ “ለ” ተደልድሎ የሚወዳደር ሲሆን ቡድኑም ባሳደገው አሰልጣኙ ሠለሞን አዳነ መሪነት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ማከናወን የጀመረ ሲሆን ከአስራ አንድ ነባር ተጫዋቾች በተጨማሪ አስራ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ግብ ጠባቂዎች አብርሃም ኃይሌ ከሸገር ፣ ሀይማኖት አዲሱ ከኮልፌ ቀራኒዮ ፣ ዱቤ ሞሉ ከኦሮሚያ ፓሊስ  ፣ በተከላካይ ቦታ ላይ ቴዎድሮስ እንዳለ ከወልድያ ፣ ታሪኩ እሸቴ ከሸገር ከተማ ፣ ተመስገን አዳሙ ከወሎ ኮምቦልቻ ፣ ፉዓድ ጀማል ከወልድያ ፤ በአማካይ ቦታ ነብዩ ንጉሴ ከሸገር ከተማ ፣ ፍቃዱ እልሁ ከ ሸገር ከተማ ፣ በድሉ መርዕድ ከኮልፌ ቀራኒዮ ፣ ቢቂላ ሲራክ ከኦሮሚያ ፓሊስ ፤ አጥቂዎች አብዱልመጂድ ሁሴን ከሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ፣ ዳንኤል በኃይሉ ከቢሾፍቱ ከተማ እና ከቤ ብዙነህ ከአምቦ ጎል ፕሮጀክት ለክለቡ ፊርማቸውን ያኖሩ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው።