በአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና የሚመሩት ቤንች ማጂ ቡናዎች የስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቅቀዋል።
በ2017 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ በምድብ “ሀ” ስር ተደልድሎ የሚገኘው ቤንች ማጂ ቡና ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ በሾመው አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና እየተመራ ለውድድር ዘመኑ ዝግጅቱን በቢሾፍቱ ከተማ ማከናወን የጀመረ ሲሆን ቡድኑም ራሱን ለማጠናከር እና ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት ከተለያዩ ቡድኖች የስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።
ከኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን የተገኘው እና የተጠናቀቀውን ዓመት በኦሮሚያ ፓሊስ ያሳለፈው አማካዩ ፋሲል አማረን ጨምሮ ፉዓድ ሙዘሚል ተከላካይ ከአዳማ ከተማ ፣ አማኑኤል ተፈራ ተከላካይ ከባቱ ከተማ ፣ ሽመልስ ቦጋለ አማካይ ከኦሮሚያ ፓሊስ ፣ ማንያዘዋል ካሳ ከጅማ አባጅፋር እና ግብ ጠባቂው ዶትን ዳንኤል ከኦሮሚያ ፓሊስ ቡድኑን መቀላቀል የቻሉ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው።
ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናት የቀድሞው የጅማ አባጅፋር እና ፋሲል ከነማ ተከላካይ የሆነውን ወንድማገኝ ማርቆስ እና ብሩክ ስህንን ለማስፈረም መቃረቡን ክለቡ አሳውቆናል።