የአሰልጣኞች አስተያየት | መቐለ 70 እንደርታ 1-1 መቻል

በምሽቱ መርሐግብር ምዓም አናብስት እና መቻሎች አቻ ከተለያዩ በኋላ የሁለቱም ክለቦች አሰልጣኞች ተከታዩን ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አድርገዋል

አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐየ –  መቐለ 70 እንደርታ

”ሁለት ሦስት ማግባት የምንችልባቸውን አጋጣሚዎች መጠቀም አልቻልንም እንጂ በመጀመሪያ አጋማሽ ጨዋታውን መጨረስ የምንችልባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ ያንን ማድረግ ስላልቻልን በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው ጠንከር ሊል ችሏል።”

አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ – መቻል

”ጨዋታ አቋርጠህ ስትመጣ የተጫዋቾች ኢንተንሲቲ ይቀንሳል፣ እስኪዋሃዱ ድረስ እንጂ በፍፁም ቡድናችን ጥሩ ነው። የምንጫወተው ጨዋታም ጥሩ ነው በግንቦት ወር አካባቢ ተገቢው ቦታ ላይ እንገኛለን።”

ሙሉ አስተያየቶቻቸውን ዩቲዩብ ቻነላችን ላይ ያገኙታል – LINK