የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-1 ፋሲል ከነማ

ፋሲል ከነማ በመጨረሻ ደቂቃ ግብ ከአዳማ ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ

“ውድድሩ ተቋርጦ ከመጀመሩ አንጻር በእንቅስቃሴ መጥፎ አልነበርንም። ተጋጣሚ ቡድን ወደ ራሱ ሜዳ ወርዶ መጫወቱ ደግሞ ትንሽ አክብዶብናል ፤ በቀይ ካርድ ሰው ማጣታቸውም ተነሳሽነታቸውን ጨምሮታል። አድቫንቴጅ ቢኖረውም የቁጥር ብልጫ ብቻውን እንድታሸንፍ አያደርግም ፤ ጉጉት እና ስሜታዊነት ታይቶብናል።”

አሰልጣኝ አብዲ ቡሊ – አዳማ ከተማ

“ከቀይ ካርዱ በፊት ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እያደረግን ነበር ካርዱ ረብሾናል። ተጫዋቹ አውቆ እንዳልተማታ ነው የማስበው። በውጤቱ ደስተኛ ነኝ። ቢኒያም ዐይተን ብዙ ስቴፕ መሄድ የሚችል ተጫዋች ነው ብዙ ይቀረዋል።”

ሙሉ አስተያየቶችን በዩቲዩብ ቻናላችን ያገኙታል – LINK