በጨዋታ ሳምንቱ ቀዳሚ መርሐግብር ኢትዮጵያ መድን ወልዋሎ ዓ.ዩን በአብዲሳ ጀማል ብቸኛ ግብ ከረቱበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
“ጠንካራ ጨዋታ ነበር ፤ በተለይ በሁለተኛው አጋማሽ ከውጤቱም አስፈላጊነት አንፃር በጣም ተቸግረን ነበር። የዛሬው ድል ለቀጣይ ጉዟችን ከፍተኛ መነሳሳትን ይፈጥርልናል።”አሸናፊ በቀለ – ወልዋሎ ዓ.ዩ
“በዛሬው ጨዋታ ከባለፈው በተሻለ ተንቀሳቅሰናል ነገርግን ተሸንፈናል። አሁንም ማጥቃታችን ትክክል አይደለም ይህን ማሻሻል ይኖርብናል።”