ቢንያም ፍቅሬ አዲስ አበባ ይገኛል

ግብፁ ክለብ እስማኤሊያ ፊርማውን አኑሮ የነበረው ቢንያም ፍቅሬ አዲስ አበባ ይገኛል።

የቀድሞው የወላይታ ድቻ አጥቂ ቢኒያም ፍቅሬ ከወራት በፊት ለግብፁ እስማኤሊያ ለመጫወት ቅድመ ስምምነት በመፈፀም ከቡድኑ ጋር ለቅድመ ዝግጅት ወደ ኳታር በማቅናት እስከ ትላትናው ዕለት ድረስ ተጫዋቹ ከእስማኤሊያ ጋር ዝግጅቱን ሲከወን ቆይቷል።

ሆኖም ክለቡ ቢንያምን ለማስፈረም ያደረገው ጥረት ዝውውሩን ፊፋ በተለያዩ ምክንያቶች ሊያፀድቀው እንዳልቻለ እና በዚህ ምክንያት ቢንያም እስማኤሊያ ጋር ያለው ቅድመ ስምምነት መቋረጡን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባቱን ወኪሉ አዛርያስ ተስፋፂሆን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።
ይህን ተከትሎ በአሁን ሰዓት ለአንድ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለብ ፊርማውን ለማኖር እየተደራደረ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ ዝውውሩ እንደሚጠናቀቅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።