ወላይታ ድቻ ሀዲያ ሆሳዕናን በማሸነፍ ከሊጉ መሪ ጋር በነጥብ ከተስካከለበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ለሶከር ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ – ወላይታ ድቻ
”ጥሩ የመከላከል ኳሊቲ አለን ከዚህ የበለጠ ማጠንከር እና መጓዝ ይጠበቅብናል። አዳዲሶችን ተጫዋቾች ከነባሮቹ ጋር ለማዋሃድ ተቸግረን ነበር ፤ አሁን እዚህ የቆየንባት ያች አስራ አምስት ቀኗ ብዙ ነገሮችን ዐይተን ቡድናችንን አስተካክለን ለመግባት ረድቶናል ፤ አሁን ወደ ቦታችን ተመልሰናል።”
አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ – ሀዲያ ሆሳዕና
”ተጫዋቾች በብዛት ተጎደተውብናል ፤ በዚያ ቦታ በተፈጠረ ክፍተት ተቆጥሮብናል። የነበረው እንቅስቃሴ ጥሩ ነው ፤ ግን ሽንፈቱ ተገቢ ነው ብዬ አላስብም። ከማጥቃት ጋር የተያያዘ የጥራት ችግር እንዳለ ተደጋጋሚ ጨዋታዎች ላይ ዐይተናል። ደረጃው ምንም አያሳስበንም።”
ሙሉውን አስተያየት ለማድመጥ LINK