ድሬዳዋን ከአዳማ ነጥብ በማጋራት ከተጠናቀቀው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገው ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ – ድሬዳዋ ከተማ
”የመድረስ ችግር የለብንም ፤ የማግባት ችግር ነው።ጨዋታዎች ገና ናቸው ፤ ለተመልካች መተኛት ሳይሆን ኳስ ብናሳይ ጥሩ ነው። አንዳንዴ ከኋላ ደፈን አድርገህ መጫወት አለብህ። ስሜታዊ ሆኜ ዳኛውን ተናግረዋለውና ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ።”
አሰልጣኝ አብዱ ቡሊ – አዳማ ከተማ
”’የግብ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር የሄድንበት መንገድ አልተሳካም እንጂ አቻ መውጣታችን አያሳፍርም።ጥንካሬያችን አንድነታችን ነው ፤ እንደቡድን ልጆች ናቸው የምትላቸውን ሰምተው በፍላጎት ነው ሚጫወቱት።”